በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በአሸባሪው ህወሓት ላይ የሚወሰደውን እርምጃ በመደገፍ ሰልፍ አደረጉ

ሐምሌ 24/2013 ( ዋልታ) – በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በአሸባሪው ህወሓት ላይ የሚወሰደውን እርምጃ በሚችሉት ሁሉ እንደግፋለን ሲሉ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ ፡፡

ኢትዮጵያዊያኑ በካርቱም ባሰሙት ድምጽ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የውጭ ጫናንና ጣልቃ ገብነትን አጥብቀው አውግዘዋል።

በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ሰልፈኞቹ የአገራቸው ጉዳይ አሳስቧቸው ለመንግስት ድጋፍ ለመስጠትና ጫናዎችን ለማውገዝ ወደ አደባባይ መውጣታቸውን አመስግነዋል ።

ሽብርተኛው ቡድን ህጻናት ፣ሴቶችን እና አረጋዊያንን በማሰለፍ እየፈጸመ ያለውን ትንኮሳ ሊወገዝ ይገባል ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።