በሱዳን ጉዳይ የመከሩት አሜሪካና የአፍሪካ ኅብረት መከሩ

ጥቅምት 17/2014 (ዋልታ) የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንትና የአፍሪከ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ፍሊክስ ቲሽኬዲ ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይቱን ተከትሎ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣው መግለጫ እንደሚጠቁመው በሱዳን የተፈጸመው መፈንቅለ መንግሥት በአገሪቱና በቀጣናው የዴሞክራሲ ሂደትና መረጋጋት ላይ ስለሚኖረው ትርጉምና ሁለቱም ወገኖች ስላላቸው የጋራ ጉዳይ ባለሥልጣናቱ መክረዋል፡፡

አሜሪካና የአፍሪካ ኅብረት፤ በኅብረቱ አደራዳሪነት በተደረሰው የ2019ኙ ሕገ መንግሥታዊ ቃልኪዳን መሰረት አገሪቱ ወደ ሲቪል መር አስተዳደር መመለስ እንዳለባት ተግባብተዋልም ነው የተባለው፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ሱዳንን ከአባልነትና ከየትኛውም የኅብረቱ መርሃ ግብሮች ተሳትፎ እንዳገዳት ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

ኅብረቱ በመሪነት ከሚሳተፍባቸው መካከል ደግሞ የታላቁ ኅዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ተጣቃሽ ነው፡፡