በሴቶች መብትና እኩልነት አያያዝ ዙሪያ ምክክር እየተደረገ ነው

የካቲት 30/2014 (ዋልታ) በህፃናትና ሴቶች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ፕላን ኢንተርንልሽናል ኢትዮጵያ ግብረሰናይ ድርጅት በሴቶች መብትና እኩልነት አያያዝ ዙሪያ ምክክር እያደረገ ነው።

በመድረኩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል መሰረት ዘላለም (ዶ/ር)፣ ሁለገብ አርቲስት ሳያት ደምሴ፣ የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ተሟጋች ናሁሰናይ ግርማ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።

በዝግጅቱ ላይ ሴቶች ድሮና ዛሬ በሚል መነሻ ሃሳብ ውይይትና ምክክር የተካሄደ ሲሆን አሁን ላይ የሴት ልጅ መብትና እኩልነት አያያዝ ከበፊቱ የተሻለ ቢሆንም ዛሬም መሻሻል እንዳለበት ተጠቁሟል።

የሴት ልጅ መብት ማርች 8 ተብሎ በተሰየመ ዕለት ተከብሮ ማለፍ ብቻ ሳይሆን በእለተ ተዕለት ሕይወት ውስጥ መታሰብ ያለበት መሆኑም ነው የተነገረው።

ከተመሰረተ 80 ዓመታት ያለፈው ፕላን ኢንተርናሽናል ግብረ ሰናይ ድርጅት ኢትዮጵያን ጨምሮ በ75 አገራት ባሉ ህፃናትና እንስቶች ማብቃት ላይ እየሰራ ይገኛል።

ፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የህፃናትና ሴቶችን መብት ለማስጠበቅ የተቋቋሙ ማኅበራትን ለማብቃት እየሰራም እንደሚገኝ ተመላክቷል።

በደምሰው በነበሩ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW