ሰኔ 10/2013 (ዋልታ) – በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በኢትዮጵያ ላይ እየተደረጉ ያሉ ያልተጋቡ ጫናዎችን በመቃወም በጄኔቭ ከተማ ሰልፍ አካሂደዋል።
ሰልፈኞቹ ካስተጋቧቸው መልዕክቶች መካከል “በኢትዮጵያ ላይ የምታሳድሩትን ያልተገባ ጫና አቁሙ፤ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘገባዎቻችሁ ሚዛናዊነትን የጠበቁ ይሁኑ፤ የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፈን አንሰጥም” የሚሉት እንደሚገኙባቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም የአሜሪካ መንግሥት በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ መካከል ለዘመናት የዘለቀውን ወዳጅነት ታሳቢ በማድረግ በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ለውጥ እንዲደግፍ እንዲሁም የሰብአዊ እርዳታ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
ሰልፉን ያስተባበሩት የአውሮፓ እና ስዊዘርላንድ “ዲፌንድ ኢትዮጵያ” ግብረ-ኃይል አባላት ሲሆኑ፣ ዝርዝር ጉዳዮችን የያዘ ደብዳቤም በወቅቱ በስፍራው ለተገኙት የአሜሪካ ፕሬዝዳት ጆ ባይደን እንዲሁም ተቀማጭነታቸውን በጄኔቭ ከተማ ላደረጉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ማስገባታቸውን ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ የተገኘነ መረጃ ያመለክታል።