በሶማሌ ክልል ለነዳጅ ድጎማ ከ4 ሺሕ በላይ ተሽከርካሪዎች ምዝገባ ተከናወነ


መስከረም 4/2015 (ዋልታ) በሶማሌ ክልል የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ የሚሆኑ ከአራት ሺሕ በላይ ተሽከርካሪዎች ምዝገባ መከናወኑን የክልሉ የንግድና ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በክልሉ ከ3 ሺሕ በላይ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎችም የነዳጅ ድጎማ አሰራር ተጠቃሚ መሆን መጀመራቸው ተገልጿል፡፡

የነዳጅ ድጎማው ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት የሚሰጡ 3 ሺሕ 375 የሚሆኑ በታሪፍ እና በስምሪት ቁጥጥር ላይ የተመሠረተ መለስተኛ፣ መካከለኛ የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች መጠቀም መቻላቸውን ቢሮው አመልክቷል፡፡

በክልሉ በተመረጡ 91 ማደያዎች ባለሀብቶችና ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች በቴሌ ብር እየተከናወነ የሚገኘውን የነዳጅ ክፍያ ሥርዓት አፈጻጸም በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

በቴሌ ብር አማካኝነት በ60 ቀናት ውስጥ 53 ሺሕ ተሽከርካሪዎች በድጎማው ተጠቃሚ መሆናቸውንና በዚህም ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ግብይት መፈጸሙን የኢትዮ ቴሌኮም ሞባይል መኒ ዲቪዢን ዋና ኃላፊ ብሩክ አዳነ ገልጸዋል።

በቴክኖሎጂ ክፍያ ሥርዓቱ ላይ የሚታየውን የግንዛቤ እጥረት ለመቅረፍ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ እየተሰራ እንደሚገኝ ቢሮው ማሳወቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW