በሶማሌ ክልል ድርቅ ለተከሰተባቸው አከባቢዎች ማቋቋሚያ 338 ሚሊየን ብር ተመደበ

ሚያዝያ 17/2014 (ዋልታ) የመስኖና ቆላማ አከባቢ ሚኒስቴር በሶማሌ ክልል ድርቅ ለተከሰተባቸው አከባቢዎች ማቋቋሚያ 338 ሚሊየን ብር መመደቡን አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ የሚተገብራቸውን የማቋቋሚያ ሥራዎች ማሳወቂያ መርኃ ግብር በጅግጅጋ ከተማ አካሂዷል።

በመርኃ ግብሩ ላይ በቆላማ አከባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በኩል በሶማሌ ክልል ድርቅ በተከሰተባቸው አከባቢዎች የማቋቋሚያ ሥራዎቹ እንደሚከናወኑ ተገልጿል።

ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በ338 ሚሊየን ብር ይከናወናልም ነው የተባለው።

በማሳወቂያ መርኃ ግብሩ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ፣ የመስኖና ቆላማ አከባቢ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ እና ሌሎች የፌዴራልና የሶማሌ ክልል የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW