በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘው ግሎኬር ፋርማ ማኑፋክቸሪንግ የመድኃኒት ምርት ጀመረ

ግሎኬር ፋርማ ማኑፋክቸሪንግ

የካቲት 30/2014 (ዋልታ) በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘው እና በመድኃኒት ማምረት እና ማዘጋጀት ሥራ ላይ የተሰማራው ግሎኬር ፋርማ ማኑፋክቸሪንግ የተሰኘው የሕንድ ኩባንያ ግንባታውን እና ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቆ በዛሬው ዕለት ምርት ጀምሯል።

በምርት ማስጀመሪያ እና የፋብሪካ ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሳንዶካን ደበበ፣ የጤና ሚኒስቴር እና ሌሎች የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የፋብሪካው የመጀመሪያው ምእራፍ 5 ሚሊዮን ዶላር የፈጀ ሲሆን በቀጣይ እስከ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት የሚጠይቁ የፋብሪካው ሁለተኛ እና ሦሥተኛ ምእራፍ ግንባታዎች ይከናወናሉ ተብሏል።

ፋብሪካው በአጠቃላይ 36 ዓይነት መድኃኒቶችን እንደሚያመርት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!