የአሸባሪው ሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ

ታኅሣሥ 11/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን አንፍሎ እና ጋዎ ቄቤ ወረዳዎች የአሸባሪው ሸኔ አባላት ከዘረፉት ሀብት እና ከተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ጋር በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የሽብር ቡድኑ አባላት ዘርፈውት ከነበረው 56 ኩንታል ቡና እና 16 የተለያዩ ጠብመንጃዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።
በቁጥጥር ስር የዋሉት የሸኔ አባላት ቡድኑ ኅብረተሰቡን በመዝረፍና በማሰቃየት ላይ እንደተሰማራ ገልጸው በጫካ የቀሩት የቡድኑ አባላት እጅ እንዲሰጡ መጠየቃቸውን ከኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
የአንፍሎ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ሳጂን ተካልኝ ባሩ በአካባቢው ዛላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ ኅብረተሰቡ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ መቀጠል እንዳበት አሳስበዋል፡፡