በቆላማና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመስኖ ግንባታዎችን ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ

ታኅሣሥ 19/2014 (ዋልታ) በቆላማና አርብቶ አደር አካባቢዎች የኅብረተሰቡን ኑሮ ደረጃ ማሻሻል እና የመካከለኛ ሰፋፊ የመስኖ ግንባታዎችን ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ሚኒስትሯ ይህን ያሉት የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር በመንግሥት ተቋማት የ100 ቀን ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ግምገማ ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡
ሚኒስቴሩ እያካሄደ ባለው ግምገማ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር የ100 ቀን ዕቅድ ትግበራ ላይ ግምገማ ተካሂዷል።
በዚህም የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በቆላማና አርብቶ አደር አካባቢዎች የኅብረተሰብ የኑሮ ደረጃ ማሻሻል እንዲሁም የመካከለኛ ሰፋፊ የመስኖ ግንባታዎችን ማሳደግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የመስኖ ልማት፣ በቆላማና አርብቶ አደር ላይ ጥሩ አፈፃፀም እየታየ እንደሚገኝ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡