በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ 146 ግለሰቦች ተለቀቁ

ታኅሣሥ 24/2014 (ዋልታ) በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከአሸባሪው ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው በቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩት ውስጥ 146 ግለሰቦች የተሀድሶ ስልጠና ተሰጥቷቸው መለቀቃቸው ተገለፀ።
በአዋጁ የሽብርተኛው ትሕነግ እና የሽብር ግብረአበሮቹ እንቅስቃሴ ደጋፊና ፈፃሚ እንደሆኑ ተጠርጥረው ከተያዙት ውስጥ የምርመራ ቡድኑ እና የፀጥታ ኮማንድ ፖስቱ ለአገር ስጋት አይሆኑም ተብለው የተለዩትን የመጀመሪያ ዙር 146 ተጠርጣሪዎች ኮማንድ ፖስቱ እንዲፈቱ ወስኗል።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ድንጋጌዎች የተጣሉ ገደቦችን በማለፍ ተጠርጥረው የተያዙ ሌሌች ተጠርጣሪዎችም በየደረጃው ጉዳያቸው ተጣርቶ ሰላማዊ መሆናቸው ሲረጋገጥ በቀጣይ እንደሚለቀቁ የክልሉን የሰላም ግንባታና የፀጥታ ቢሮ ጠቅሶ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።