በብላቴ የልዩ ዘመቻ ማሰልጠኛ የወታደሮች ምርቃት

በብላቴ የወታደሮች ምርቃት

መስከረም 3/2014 (ዋልታ) የብላቴ የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል በመሰረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አባላት አስመረቀ፡፡

ተመራቂ ወታደሮቹ በውጊያ ቴክኒክ፣ በአካል ብቃት እንደዚሁም በሌሎችም መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ በንድፈ ሃሳብ እና በተግባር የታገዘ ሥልጠና ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

እንደኢቢሲ ዘገባ ተመራቂ የሰራዊት አባላቱ የሚሰጣቸውን ማንኛውም ግዳጅ በብቃት በመወጣት አገርን ከውስጥ እና ከውጭ ወራሪ ለመጠበቅ ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተደድር ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተገኝተዋል።