በብራዚል እና አርጀንቲና በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸነፉ


ነሐሴ 16/2014 (ዋልታ) በብራዚል ሪዮ ዲ ጄኔሮ እና በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በተካሄዱ የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ማሸነፍ ችለዋል፡፡

በወንዶች የግማሽ ማራቶን ውድድር አሰፋ በቀለ በ1 ሠዓት ከ3 ደቂቃ ከ52 ሰከንድ በመግባት ቀዳሚ በመሆን ሲያሸንፍ በሴቶቹ ደግሞ መስታወት ፍቅሬ 1 ሠዓት ከ13 ደቂቃ ከ4 ሰከንድ በመግባት አሸንፋለች።

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ፋንቱ ገላሳ በሴቶች ግማሽ ማራቶን በ3 ሰኮንድ ዘግይታ 1 ሠዓት ከ13 ደቂቃ ከ7 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች፡፡

በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድርም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል።

በወንዶች ግማሽ ማራቶን ገርባ በያታ 1 ሠዓት ከ29 ሰከንድ በመግባት ሲያሸንፍ የሀገሩ ልጅ ድንቅዓለም አየለ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል።

በሴቶች ደግሞ አታላይ አንሙት 1 ሠዓት ከ7 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ስትወጣ ዘውዲቱ አደራው ደግሞ በውድድሩ 5ኛ እንዲሁም ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አዲስዓለም በላይ 9ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቃቸውን ኤፍቢሲ ከሪዮ እና ቦነስ አይረስ ማራቶን ምንጮች ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW