በተስፋ ብርሃን የምግባ ማዕከል ማዕድ ማጋራት

መስከረም 2/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ሱማሌ ተራ በሚሰኘው አካባቢ የሚገኘው የአሙዲ ተስፋ ብርሃን የምግባ ማዕከል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ከ2 ሺሕ በላይ ለሆኑ ወገኖች የማዕድ ማጋራት አካሄደ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሥነ ሥርዓቱ ላይ በመገኘት በዓልን ከእናንተ ጋር ማክበር በመቻሌ ደስተኛ ነኝ ብለዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጀማል አህመድም ተገኝተዋል፡፡