በቱርክ-አፍሪካ ጉባኤ የኢትዮጵያ ልዑክ ከፍተኛ ሥራ መሥራቱ ተገለፀ

ታኅሣሥ 11/2014 (ዋልታ) በቱርክ የአፍሪካ ጉባኤ የኢትዮጵያ ልዑክ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ሥራ መስራቱን መንግሥት አስታወቀ፡፡

በ3ኛው ጉባኤ ቱርክም በአፍሪካ ያላትን ወዳጅነት የበለጠ አጠናክራለች ሲል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ገልጿል፡፡

እንደሚኒስትር ዴኤታዋ ሰላማዊት ካሳ መግለጫ አፍሪካዊያን በራሳቸው መቆም እንዲችሉና አፍሪካ በዓለም ዐቀፍ መድረኮች ላይ ውክልና እንዲኖራት በማድረግ ረገድ ለተነሱ የሐሳብ ልውውጦችና መግባባቶች የጉባኤው ሚና ከፍተኛ ነበር፡፡