በቴክኒክ ደንብ ትግበራ ሥርዓት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

ሐምሌ 5/2014 (ዋልታ) የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና በተቆጣጣሪ ተቋማት መካከል በቴክኒክ ደንብ ትግበራ ሥርዓት ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

የቴክኒክ ደንብ ሥራ በህግ ማዕቀፍ የተደገፈ ሲሆን የአሰራር ችግሮችን የመቅርፍ አቅም እንዳለው በመድረኩ ተመላክቷል።

በተጨማሪም የቴክኒክ ደንብ ሥራ የተቀላጠፈ የአሰራር ሥርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል ሲሆን በዛው ልክ ተጠያቂነትን ማስፈን የሚያስችል ሥርዓትን ለመዘርጋት ያግዛል ነው የተባለው።

በዚህም መንግሥት የንግድ ሥርዓቱ የተሳለጠ እንዲሆን ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኘ ነው የተመላከተው።

እየተካሄደ ባለው መድረክ በቴክኒክ ደንብ አተገባበር ላይ ሰነድ ቀርቦ ወይይት እየተካሄደ ነው፡፡

በሜሮን መስፍን