በቴፒ ከተማ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ፕሮግራም ተካሄደ

በቴፒ ከተማ የጎዳና ላይ ኢፍጣር

ሚያዝያ 21/2014 (ዋልታ) በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ የአብሮነት የጎዳና ላይ ኢፍጣር ፕሮግራም ተካሄደ።

የሃይማኖት አባቶች ኅብረትና የሀገር ሽማግሌዎች ጥረት በማድረግ በከተማዋ የነበረውን ውጥረትና ግጭት በማርገብ ዳግም ወደ ሰላሟ መልሷታልም ተብሏል።

በሸካ ዞን የኪ ወረዳ የቴፕ ከተማ ሙስሊሞች ለሦስት ዓመታት በከተማዋ የነበረው ውጥረትና ግጭት ረግቦ በአደባባይ ማዕድ መጋራት ከሌሎች እምነቶች ጋር በሠላም እና ትብብር መወዳጀት በመቻለቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የቴፕ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ገላቲያስ ሻሜ በከተማዋ ሠላም ሰፍኖና በእምነት ተቋማት ኅብረት መፈጠሩን ጠቅሰው የኢፍጣር ፕሮግራም ያዘጋጁ አካላትን በጎ ተግባር አመስግነዋል።

የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አበበ ማሞ በታላቁ የረመዳን ወር ሙስሉሙ ሰደቃን በማውጣት ሚስኪኖችን አስታውሶ በአብሮነት እንዳሳለፈ ሁሉ የሀገር አፍራሽነት ተልዕኮ ያላቻውን ፀረ ሠላም ኃይሎችና በአንድነታችን ላይ የሚቃጡትን እኩይ ተግባር በጋራ ልንከላከል ይገባል ብለዋል።

በቴፒ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው የጎዳና ኢፍጣር በሠላም ተጠናቋል።

አክሊሉ ሲራጅ (ከቴፒ)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!