በትምህርት ዘርፉ የተጀመሩ የማሻሻያ ተግባራትን ከግብ ለማድረስ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ተጠየቀ

ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር)

ሐምሌ 8/2014 (ዋልታ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) የተጀመሩ የማሻሻያ ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ሁሉም አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

ለሚኒስቴሩ አመራሮችና ሰራተኞች ሲሰጥ በነበረው የስልጠና ማጠቃለያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ሚኒስትሩ በቀጣይ የሚጠበቀውን ውጤት ለማምጣት ሥራዎችን በራስ አቅምና ተነሳሽነት መስራት እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡

በስልጠናው በአመራሮችና ሰራተኞች መካከል የጋራ መግባባት መፍጠር እነንደቻለና ይህም በትምህርት ዘርፍ የተጀመሩ የማሻሻያ ሥራዎች ከዳር ለማድረስና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ መነሳሳትን የፈጠረ ነው ተብሏል።

የስልጠናው ዓላማም የትምህርት ሴክተሩ ሥራውን በአዲስና በተሻለ መንገድ እንዲሰራ፣ ሠራተኛው ሙያውን አክብሮ ሥራውን በጥራትና በብቃት ለመስራት እንዲዘጋጅ እንዲሁም አመራሩ ለውጡን ከግብ ለማድረስ በቁርጠኝነት እንዲነሳ የሚያስችል እንደነበረም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW