በቶኪዮ ማራቶን ኢሉድ ኪፕቾጌ 1ኛ ሲወጣ ኢትዮጵያዊው ታምራት 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀ

የካቲት 27/2014 (ዋልታ) በቶኪዮ ማራቶን ኢሉድ ኪፕቾጌ ድል ሲቀናው ኢትዮጵያዊው ታምራት ቶላ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀ፡፡

በወርልድ አትሌቲክስ የፕላቲንየም ደረጃ ከተሰጣቸው የማራቶን ውድድሮች መካከል አንዱ የሆነው የቶኪዮ የማራቶን ዛሬ ተካሂዷል፡፡

የተካሄደ ሲሆን በሁለቱም ፆታ የርቀቱ ፈጣን እና የክብረወሰን ባለቤት የሆኑ አትሌቶች በተሳተፉበት ውድድር የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቱ ኢሊድ ኪፕቾጌን የሚያቆመው አልተገኘም፡፡

አትሌቱ ባለፉት አራት ተከታታይ ታላላቅ የማራቶን ውድድሮች ድል የቀናው ሲሆን ዛሬ ደግሞ በጃፓን ቶኪዮ ክብሩን አስጠብቋል፡፡
ርቀቱን በበላይነት ሲፈፅም 2 ሰዓት ከ02 ደቂቃ ከ40 ሰክንድ ፈጅቶበታል፡፡

አሞስ ኪፕሩቶ ከኬንያ 2ኛ ታምራት ቶላ 3ኛ ሹራ ቂጣታ 5ኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቁ አትሌቶች ናቸው፡፡

በሴቶች በተካሄደው ውድድር ኬንያዊቷ ብሪጅድ ኮስጌይ በአሸናፊነት ስታጠናቅቅ አሸት በከሪ እና ጎትቶም ገብረ ስላሴ ተከታታይ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ጨርሰዋል፡፡