በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ አባላት ለተፈናቀሉ ወገኖች የ23 ሺሕ ዶላር ድጋፍ አደረጉ

ታኅሣሥ 1/2014 (ዋልታ) በኬኒያ ናይሮቢ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ አባላት ለተፈናቀሉ ወገኖች ሰብዓዊ እርዳታ የሚውል 23 ሺሕ የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አድርገዋል።

የገንዘብ ድጋፉን የኮሙዩኒቲ ተወካይ መስፈን እጅጉ በኤምባሲው ተገኝተው አስረክበዋል።

በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ አባላት ኢትዮጵያ ወገናዊ ጥሪ ባቀረበችላቸው ጊዜያት ሁሉ በሀገር ፍቅር ስሜት ለሚያደርጉት ሁለንተናዊ ድጋፍ አመስግነዋል።

ሚሲዮኑም ከኮሙዩኒቲ አባላቱ ጋር በቅርበት ተባብሮ እንደሚሰራም ገልፀዋል።

በናይሮቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በ2013 በጀት ዓመት ለሰብዓዊ ድጋፍ፣ ኮቪድ-19ን ለመከላከል እና ልሎች ሀገራዊ ጥሪዎች የ250 ሺሕ የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ ማድረጋቸውን በኬኒያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።