በኔዘርላንድስ ለሽያጭ ቀርበው የነበሩ የኢትዮጵያ ቅርሶች ተመለሱ

ሰኔ 25/2013 (ዋልታ) – በኔዘርላንድስ ጨረታ ላይ ለሽያጭ ቀርበው የነበሩ ሶስት ጥንታዊ መጻሕፍት የኢትዮጵያ ቅርሶች የኔዘርላንድ ኤምባሲ መረከብ መቻሉን የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳው አስታወቁ።

ቅርሶቹ ሊመለሱ የቻሉት የኔዘርላንድ ኤምባሲ ባደረገው ጥረት እና የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑ የኔዘርላንድስ ተወላጅ ባደረጉት ጥረት መሆኑንም ገልጸዋል።

ቅርሶቹ የዛሬ ሳምንት በኔዘርላንድስ ለጨረታ ሊቀርቡና ሊሸጡ እንደነበር በኔዘርላንድስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

ኤምባሲውም የጨረታ ሂደቱ እንዲቋረጥ ጥያቄ አቅርቦ ተቀባይነት ማግኘቱን ገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎም ቅርሶቹን የተረከበ ሲሆን፣ ቅርሶቹ ከ15ኛው ክፍለ ዘመን በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ እንደሆኑ ይታመናል፡፡