የፀረ ሙስና ቀን በጎንደር ከተማ እየተከበረ ነው

“የትውልድ የስነ ምግባር ግንባታን በተጠናከረ ዲሲፕሊን በመምራት ሌብነትን እና ብልሹ አሰራርን በመታገል የብልፅግና ጉዟችንን እናፋጥናለን” በሚል መሪ ሃሳብ በዓለም ለ17ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ16ኛ ጊዜ የፀረ ሙስና ቀን  በጎንደር ከተማ እየተከበረ ነው።

በበዓሉ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በዓሉ በጎንደር ከተማ መከበሩ ከትህነግ መወገድ በኋላ አማራ ክልል ሰላም መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል።

የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፀጋ አራጌ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ በሙስና በአለም 96ኛ፤ በአፍሪካ ደግሞ 16ኛ መሆኗን ጠቅሰው፣ ይህም ትልቅ የፀረ ሙስና ንቅናቄ የሚጠይቅ ነው ብለዋል።

በበዓሉ የክብር እንግዳ የሆኑት  የህዝብ ተወካዮች ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የተጀመረው የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ ስራ ሙስናን ለመዋጋት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልፀው፣ ለፀረ ሙስና ትግሉ ምክር ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

በዓሉ በሙስና ዙሪያ የሚቀርቡ ሰነዶች ላይ ውይይት ተደርጎ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡

(በሀብታሙ ገበየሁ)