መስከረም 19/2014 (ዋልታ) የአማራ ክልል ምክር ቤት የክልሉን የ2014 ዓ.ም በጀት 80 ቢሊየን 104 ሚሊየን 669 ሺሕ 397 ብር እንዲሆን አጽድቋል።
የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣ 7ኛ ዓመት 18ኛ መጨረሻ ጉባኤ በዛረው ዕለት አካሂዷል፡፡
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር የአማራ ክልል በአሸባሪው ትህነግ በተከፈተበት ጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም ሰፊ ሥራ እንደሚጠይቀው ተናግረዋል።
በመሆኑም ክልሉ በሚያመነጨው ልክ ገቢ መሰብሰብ አለበት ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።
የሽብርተኛው ትህነግን ወረራ መመከት እና ዜጎችን መልሶ ማቋቋም ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሠራ ርእሰ መሥተዳድሩ አስታውቀዋል፡፡