በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ ጅግጅጋ ገባ

ጥር 25/2014 (ዋልታ) በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ጅግጅጋ ከተማ ገባ።
የልዑካን ቡድኑ ጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ አቀባበል ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ልዑኩ ወደ ስፍራው ያቀናው በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ መሆኑ ታውቋል።
የአማራ ክልል፤ በኦሮሚያ ክልል ጎጂና ቦረና አካባቢዎች በድርቅ ለደረሰው ጉዳት በትናንትናው እለት የእንስሳት መኖ ድጋፍ ማድረጉ ይታወቃል።