በአማራ ክልል በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ጥር 30/2014 (ዋልታ) በአማራ ክልል ከወልዲያ ወደ ባሕርዳር በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 17 ሺሕ 804 የክላሽ ጥይት ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
በሕገወጥ የመሳሪያ ዝውውሩ የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች የሴሌዳ ቁጥሩ 24071 አማ በሆነ ፒካፕ ተሽከርካሪ ጥይቶቹን በድብቅ ይዘው ሲያጓጓዙ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ይደረግ በነበረው ክትትል ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመተባበር በባሕርዳር ከተማ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።
በተመሳሳይ መነሻውን ከአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ አካባቢ በማድረግ ወደ ደብረ ብርሃን በመጓዝ ላይ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2-67339 አአ የሆነ ፒካፕ ተሽከርካሪ በሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ተጠርጥሮ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ይደረግ በነበረ ክትትል ሸዋሮቢት ከተማ ጡዚ በተባለ ኬላ 1 ብሬን ከ12 መስል ጥይት ጋር፣ 3 ክላሽ ከ8 ሺሕ 714 ጥይት ጋር፣1 ኤፍ ዋን ቦምብ እና 1 የጭስ ቦምብ ተይዟል፡፡
በድርጊቱ የተጠረጠሩ 5 ግለሰቦችም ከሕገወጥ የጦር መሣሪያዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!