በአማራ ክልል በኅልውና ዘመቻ ለተሳተፈ የጸጥታ መዋቅር የእውቅናና ምስጋና መርኃግብር እየተካሄደ ነው

ግንቦት 2/2014 (ዋልታ) የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት “በህግ ማስከበርና በኅልውና ዘመቻው የተከፈለ መስዋእትነት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና አንድነት” በሚል መሪ መልእክት በኅልውና ዘመቻው ተሳትፎ ላደረገው የጸጥታ መዋቅር የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም እየተካሄደ ነው።

በእውቅና እና የምስጋና መርኃ ግብሩ ላይ ለሕዝብ ሰላምና አንድነት ሲሉ ክቡር መስዋእትነት የከፈሉ ጀግኖች ይዘከሩበታል ተብሏል።

በጀግንነት ተፋልመው ሕዝባቸውን ከወረራና የከፋ መከራ የታደጉ ጀግኖችም ለትውልዱ በሠሩት አኩሪ ገድል እንደሚዘከር ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!