በአማራ ፖሊስ ኮሚሽን አዘጋጅነት የምክክር መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ነው

መጋቢት 4/2014 (ዋልታ) በአማራ ፖሊስ ኮሚሽን አዘጋጅነት እና በኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ የሚመራው የምክክር እና የውይይት መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ ከህግ ማስበር ዘመቻ እስከ ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት ድረስ የነበረው የሰራዊቱ ሚና የሚገመገምና የቀጣይ አቅጣጫዎች የሚቀመጡ መሆኑን ከአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።