በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው

መጋቢት 01/2013 (ዋልታ) – በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጣልቃ ገብነትን እና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን በመቃወም በዋሽንግተን ዲሲ ሰልፍ እያካሄዱ ይገኛሉ።

“አንድነት ለኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል በዋሽንግተን ዲሲ ሰልፉ የተካሄደ ሲሆን በነገው ዕለትም በኒውዮርክ ሌላ ሰልፍ ይደረጋል ተብሏል።

የዋሽንግተን ዲሲ ሰልፍ ተሳታፊዎች የተለያዩ መልዕክቶችን በመያዝ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

የውጭ አገር ሚድያዎች የትግራይ ክልል መልሶ ለመገንባት እና የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ የሚከናወነውን ተግባር እውቅና ሳይሰጡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ላይ እንደሚገኙ በሰላማዊ ሰልፉ ተንጸባርቋል።