በአሸባሪው የወደሙ ትምህርት ቤቶች የመልሶ ግንባታ ንድፍ ተጠናቀቀ

ጥር 24/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኅበር በአሸባሪው ትሕነግ የወደሙ የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች የመልሶ ግንባታ ንድፍን አጠናቆ ለትምህርት ሚኒስቴር አስረከበ።

የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኅበር በሰሜን ኢትዮጵያ የወደሙ ትምህርት ቤቶች መልሶ ግንባታ አካል የሆነውን የንድፍ ቀረጻ ሥራ ማጠናቀቁን ከማኅበሩ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

ማኅበሩ ለአዲሱ የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ያዘጋጀውን የንድፍ ቀረጻ ሰነድ በማኅበሩ ፕሬዝዳንት አማኑኤል ተሾመ አማካኝነት ለትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አስረክቧል።

የንድፍ ቀረጻው 6 ሳምንታትን የፈጀ ሲሆን በተመረጡ ቦታዎች ለሚከናወኑ ዝርዝር ሰነዶች የማኅበሩ አባላት ዝግጁ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።