በአሻባሪው ሕወሓት የተገደሉ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላትን የሚዘክር የሻማ ማብራት ሥነ-ስርዓት ተካሄደ

ሐምሌ 24/2013 (ዋልታ) – በአሻባሪው ሕወሓት በተለያዩ የትግራይ ከተሞች የተገደሉ ከ100 በላይ  የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላትን የሚዘክር የሻማ ማብራት ሥነ-ስርዓት በመስቀል አደባባይ ተካሄደ።

ህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ጸብሎ መሰየሙ ይታወሳል፡፡

አሸባሪው ህወሓት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ከወጣ በሁዋላ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር ሰርታችሁዋል፤ ተባብራችሁዋል በሚል በሀገር ሰላም የተገደለችውን ነፍሰጡር አመራር ጨምሮ ከ100 በላይ ሰዎችን በአደባባይ በግፍ ገድሏል።

በዚህ የሻማ ማብራት ስነ ስርአት ላይ ዶ/ር አብረሃም በላይን ጨምሮ፤ የጊዚያዊ አስተዳድሩ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሚልዮን ኣብርሃ፣ የትዴፖ ሊቀመንበር ዶ/ር አረጋዊ በርሀ ፣ የጊዚያዊ አስተዳድሩ አመራሮች፣ የተለያዩ ፓርቲ አመራሮች እናየትገራይ ተወላጆች ተገኝተዋል ሲል የዘገበው ኢፕድ  ነው፡፡