በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እና በኦሮሚያ ልዩ ዞን አጎራባች ከተማና ወረዳ አስተዳደሮች የሕዝብ ለሕዝብ ውይይት እየተደረገ ነው

ታኅሣሥ 1/2014 (ዋልታ) በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር እና በፊንፊኔ ዙሪያ በኦሮሚያ ልዩ ዞን አጎራባች ከተማና ወረዳ አስተዳደሮች የሕዝብ ለሕዝብ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

በውይይት መድረኩ በሕዝብና በፀጥታ ኃይሉ በተደረገ የቅንጅት ስራ ለሽብር ስራ ሊውሉ የነበሩ በርካታ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

በዚህም በጋራ የብርበራ ሥራዎች በመሰራታቸው ለጥፋት ሊውሉ የነበሩ ክላሽ፣ ሽጉጥ፣ ቦንብና ሌሎች ተቀጣጣይ ገመዶች መያዝ መቻላቸው ታውቋል።

ይህ የሕዝብ ለሕዝብ መድረክ ተጠናክሮ በመቀጠል ሽብርተኞችንና ፀጉረ ልወጦችን ማጋለጥ ላይ ሊሰራ እንደሚገባ ተነግሯል።

ከዚህ ቀደም ሕዝብ ከፀጥታ አካላት በጋራ በመስራት ህገወጥ የመሬት ወረራን መግታት እንደተቻለው ሁሉ የአሸባሪዎች ትሕነግና ሸኔ ድብቅ ሴራዎች የሚያስፈፀሙ አካላትን ማጋለጥ ይገባልም ተብሏል።

በዙፋን አምባቸው