በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የጎዳና ላይ አፍጥር እየተካሄደ ነው

ሚያዝያ 20/2014 (ዋልታ) የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ “ፆመን አብረን እናፍጥር” በሚል የጎዳና ላይ የአፍጥር መርኃ ግብር በማካሄድ ላይ ይገኛል::
የረመዳን የፆም ወር የመተጋገዝ እና የመደጋገፍ ወር ነው በሚል ድጋፍ ለሚሹ የእስልምና እምነት ተከታዮች እየተካሄደ ባለው የማእድ ማጋራት መርኃ ግብር አብሮነትን የሚያጎለብቱ እሴቶችን ማጠናከር ይገባል ተብሏል::
ከአፍጥር መርኃ ግብሩ ባለፈ ድጋፍ ለሚሹ 300 የእምነቱ ተከታዮችም ድጋፍ ተደርጓል::
በሔብሮን ዋልታው
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!