በአቋም መለኪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የኡጋንዳ አቻውን 1 ለ 0 አሸነፈ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ነሐሴ 13/2014 (ዋልታ) በአቋም መለኪያ ጨዋታ ከኡጋንዳ አቻው ጋር የተጫወተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የኡጋንዳ አቻውን 1 ለ 0 አሽንፏል፡፡

የብሔራዊ ቡድኑን የአሸናፊነት ጎል የፋሲል ከነማው የመሐል ተጫዋች በዛብህ መለዮ በ93ኛው ደቂቃ ላይ ማስቆጠር ችሏል፡፡

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በቀጣይ እሁድ ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታቸውን እንደሚያከናውኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ቀድም ሲል በአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮንሺፕ (ቻን) ውድድር ደቡብ ሱዳንን ያሸነፈ ሲሆን ከሩዋንዳ ለሚጠብቀው የደርሶ መልስ ጨዋታ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW