በአትላስ ሆቴል ለሶስት ዓመታት አልጋ ተከራይቶ የሽብር ድርጊት ሲፈጽም የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

ኅዳር 16/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 በሚገኘው አትላስ ሆቴል ውስጥ ለሶስት ዓመታት አልጋ ተከራይቶ የሽብር ድርጊት ሲፈጽም የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ዋልታ ከፀጥታና ደኅንነት ምንጮች ያገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ተጠርጣሪው ከሽብርተኛው ሸኔ ጋር በህቡዕ በመገናኘት ተልዕኮዎችን ሲያስተባብር ነበር፡፡

ተጠርጣሪው ባረፈበት ሆቴል ውስጥ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ አደንዛዥ ዕፅ፣ ሶስት ኮምፒዩተሮች፣ ሁለት ፕሪንተሮች፣ ሰባት የተለያዩ ማህተሞች፣ አንድ ላፕቶፕ እና አንድ ትልቅ ማይክ ተገኝቷል።

እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያዎች ለመልቀቅ ያዘጋጀቸው የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ሰነዶች ከሁለት ግብረአበሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን ለመረጃው ቅርበት ያላቸው ምንጮች አመልክተዋል።