በአውስትራሊያ የሚኖሩ ዳያስፖራዎች ለህልውና ዘመቻው ማጠናከሪያ የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ

በአውስትራሊያ ሜልቦርን የሚኖሩ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ተወላጆች አሸባሪው ትህነግ በፈጸመው ወረራ በአማራ ክልል በጦርነቱ ለተጎዱ ዘማች ቤተሰቦች እና ለህልውና ዘመቻ ማጠናከሪያ 44 ሺህ 157 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉን ላሰባሰቡት የማኅበሩ አባላት እና ድጋፍ በማድረግ አስተዋጽኦ ላደረጉ በአውስትራሊያ ሜልቦርን የሚኖሩ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ተወላጆች የአማራ ክልል መንግስት አመስግኖ፤ ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርቧል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡