በአዲስ አበባ ተጀምሮ የሚጠናቀቀው ፕሮጀክት ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ሰኔ 12/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ተጀምሮ የሚጠናቀቀው ፕሮጀክት ነው ሲሉ ገለጹ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይህን ያሉት በአዲስ አበባ ከተማ ለሕዝባዊ የሠላም ሠራዊት ዕውቅና የመስጠት መርኃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
ከንቲባዋ በንግግራቸው አዲስ አበባ የሰላም ፣ የአንድነትና የአብሮነት ከተማ መሆንዋ ትቀጥላች ሲሉ ገልፀዋል።
በኅልውና ዘመቻ ወቅት አዲስ አበባ ተከባለች ለሚሉ የሰላም ሠራዊቱ ከተማወን በሰላም ዘብ ከቧት ሰላሟን አረጋግጧል ነው ያሉት ከንቲባዋ።
ይህንን አንድነት ደግሞ በልማቱ በመድገም ሠራዊቱ የከተማወን ልማት እብዲያረጋግጥ ጠይቀዋል።
በዚሁ ግዜ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሕዝባዊ ሠራዊቱ በኅልውና ትግሉ ወቅት ከሠራዊቱ ጋር በቅንጅት በመስራት ላበረከቱት አስተዋፅኦ እውቅና ሰጥተዋል።
በሰለሞን በየነ