በአዲስ አበባ ከተማ በነገው ዕለት ሰልፍ እንደሚካሄድ ተገለጸ

ሐምሌ 14/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የህዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር የውሃ ሙሌት መጠናቀቁንና ከመከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናቸውን ለመግለጽ በነገው ዕለት ሰልፍ እንደሚያካሂዱ ተገለጸ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አብዲ ፀጋዬ በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቅን በማስመልከት እና በህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ የሚገኘውን የመከላከያ ሰራዊት ጎን መሆኑን ለመግለፅ በነገው ዕለት ከጠዋቱ 1፡00 ጀምሮ መዲናዋ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡

በሰልፉ ላይም ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የከተማው ነዋሪዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃሉ፡፡

(በአመለወርቅ መኳንንት)