በአዲስ አበባ ከተማ የአገር መከላከያ ሰራዊትን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት እየተደረገ ነው

ጥቅምት 25/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ የአገር መከላከያ ሰራዊትን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች በአበበ ቢቂላ ስቴድየም ሽኝት እየተደረገላቸው ነው።

በዛሬው እለት ከአዲስ አበባ የግንባሩን ህዝባዊ ዘመቻ ለመምራት በአዲስ ምእራፍ ከተመደቡት መካከል 363 አመራሮች የአሸባሪውን ሕወሓት ቡድን ለመፋለም የከተማውን ዘማች ወጣት እየመሩ የሚዘምቱ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 38ቱ ሴት አመራሮች መሆቸውን ከአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በሽኝት መርኃግብሩ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡