በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ የፖሊዮ ክትባት ይሰጣል

ሚያዝያ 28/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት ሁለተኛው ዙር የፖሊዮ ክትባት በዘመቻ ይሰጣል፡፡
በኢትዮጵያ የልጅነት ልምሻን ለመከላከል የሚያስችል ክትባት እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት በሁለተኛ ዙር እየተሰጠ ይገኛል።
በመዲናዋም የክትባት ዘመቻው ከዛሬ ሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ቤት ለቤት እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡
በመሆኑም ወላጀች ወይም አሳዳጊዎች ህጻናትን በማስከትብ ከሚደርስባችው የአካል ጉዳትና የጤና ችግር በመታደግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መጠየቁን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል::

ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!