በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኝ የሠራዊት ክፍል ለተለያዩ መኮንኖች የማዕረግ ዕድገት ሰጠ

ጥር 23/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኝ የሠራዊት ክፍል በሥራ አፈጻፀማቸው ውጤታማ ለሆኑ እና የቆይታ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ መስመራዊ እና ከፍተኛ መኮንኖች የማዕረግ ዕድገት መስጠቱ ተገለጸ።

የሠራዊት ክፍሉ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ጌታሁን ካሳዬ “ከአንድ ማዕረግ ወደ ሌላኛው የማዕረግ ዕድገት ስትሻገሩ ድርብ ኃላፊነትን እየተቀበላችሁ መሆኑን አውቃችሁ ለምትመሩት ክፍል ምሳሌ በመሆን የአመራር ሚናችሁን በቁርጠኝነት መወጣት ይጠበቅባችኋል” ብለዋል፡፡

በዕለቱ ከተሾሙት መካከል ሻለቃ አሰፌ ጉብሳ እና መቶ አለቃ ዶሻ ዶላ በሰጡት አስተያየት የተሰጣቸው የማዕረግ ዕድገት ከሕዝብ እና መንግሥት ለተጣለውን ትልቅ ሀገራዊ አደራ በታማኝነት እና በቁርጠኝነት ለማገልገል ይበልጥ እንደሚያነሳሳቸው መናገራቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።