በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግሮችና የመፍትሄ አማራጮች ዙሪያ ምክክር ተደረገ

ሐምሌ 2/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግሮችና የመፍትሄ አማራጮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡

በትናንትናው እለት በተካሄደው በዚህ ውይይት በከተማዋ ያሉ የትራንስፖርት ችግሮችን ለመፍታት ከከተማ አስተዳደሩ እንዲሁም ከሚኒስቴሩ ተወካዮች በተገኙበት የተለያዩ የአጭርና የረጀም ጊዜ የመፍትሄ አማራጮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት በተለይ አሁን ያለውን የትራንስፖርት እጥረት ለመቅረፍ በጊዜያዊነት የፐብሊክ ባሶች ወደ ትራንስፖርት ስምሪት የሚገቡበትን የመፍትሄ አማራጭ ለመጠቀም ስምምት ላይ የተደረሰ ሲሆን የድጋፍ ሰጪ አውቶብሶችም ጉዳይ የመፍትሄው አካል እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በቀጣይ የሚተገበሩ መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጡ ዘመናዊ የከተማ ትራንስፖርት አማራጮች ላይም ምክክር መደረጉን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW