በአዲስ አበባ የኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ ክትባት ከዛሬ ጀምሮ እስከ ኅዳር 15 ይሰጣል

ኅዳር 6/2014 (ዋልታ) የኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ከኅዳር 6 እስከ ኅዳር 15/2014 ዓ.ም በመንግስት የጤና ተቋማት እና በጊዜያዊ የክትባት መስጫ ተቋማት እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ ለ10 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የክትባት ሳምንት ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በላይ የሆኑ ህፃናትን ስለሚያካትት ወላጆች የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር ልጆቻቸውን እንዲያስከትቡ ጠይቀዋል።

በከተማ አስተዳደር ደረጃ እስከአሁን በአዲስ አበባ ከግማሽ ሚሊየን በላይ የሚደርሱ ዜጎች የተከተቡ ሲሆን በዚህ የኮቪድ 19 የክትባት ዘመቻ 1 ሚሊየን የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ይቻል ዘንድ 777 የሚሆኑ የክትባት ቡድኖች አገልግሎት ለመስጠት መሰማራታቸው ተገልጿል።

በቁምነገር አሕመድ