በአዳማ የመከላከያ ሰራዊትን የሚዘክር የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

ጥቅምት 24 /2014 (ዋልታ) በአዳማ ከተማ በአገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ የደረሰውን ክህደት የሚዘክር የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ተካሄደ።
የከተማዋ ነዋሪዎች ‹‹ አልረሳውም! እኔም ለሀገሬ ሰራዊት ነኝ›› በሚል መሪ ቃል በታሰበው ቀን ላይ በመሳተፍ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነት አረጋግጠዋል።
በአገር መከላከያ ሰራዊቱ ላይ የደረሰው ጥቃት በታሪክ ውስጥ የማይረሳ ነው ሲሉም ተናግረዋል። በአገር ላይ አስነዋሪውን ድርጊት የፈፀሙ አካላት የእጃቸውን እስኪያገኙ እንደሚፋለሙም ነው ነዋሪዎቹ ያረጋገጡት፡፡
በሚልኪያስ አዱኛ (ከአዳማ)