በአፈፃፀማቸው ምስጉን የሆኑ ሰራዊት አባላት ማዕረግ ተሰጠ

መስከረም 30/2014 (ዋልታ) በኢፌዴሪ አየር ኃይል ምስራቅ አየር ምድብ በስራ አፈፃፀማቸው ምስጉን ለሆኑና የመቆያ ጊዜያቸውን በጥሩ ወታደራዊ ዲሲፒሊን ለሸፈኑ የምድቡ ሰራዊት አባላት ማዕረግ ተሰጠ።
የምስራቅ አየር ምድብ አዛዥ ኮ/ል አበበ ለገሰ አየር ምድቡ ህግን በማስከበር ዘመቻ ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በግንባር ቀደምትነት በመሳተፍና የህወሓት አሸባሪ ቡድንን በመደምሰስ አኩሪ ጀብድ ፈፅሟል ብለዋል።
ተሿሚዎች በተሰጣችሁ የማዕረግ ሹመት በመበረታታት አሸባሪ ቡድኑን ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት በሚደረገው ቀጣይ የህልውና ዘመቻ ትልቅ ግዳጅ ይጠብቃችኋል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡