በአፋር በ200 በላይ ንጹሀን ዜጎች ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ እንዳሳሰበው ዩኒሴፍ ገለጸ


ነሀሴ 3/2013 (ዋልታ) –
በአፋር በ200 በላይ ንጹሀን ዜጎች ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ እንዳሳሰበው ዩኒሴፍ ገለጸ ።

ዩኒሴፍ በያዝነው ሳምንት በአፋር ክልል በጤና ጣቢያ እና በትምህርት ቤት ወስጥ ተጠልለው የነበሩ 100 ህጻናትን ጨምሮ ከ200 በላይ ዜጎች ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ እንዳሳሰበው ገልጿል፡፡

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ በግጭቱ ተፈናቅለው ለነበሩ ዜጎች ሊውል የነበረ የዕርዳታ እህል መውደሙንም ነው የገለጸው፡፡