በአፋር ክልል ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ተደረገ

ጥር 25/2014 (ዋልታ) የኢንዱስትሪ፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴሮች እና ተጠሪ ተቋማት በአፋር ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ከተጠሪ ተቋማት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እንዲሁም የኢትዮጵያ ሲሚንቶ አከፋፋዮች ማኅበር ጋር በመሆን ነው ድጋፍ ያደረጉት፡፡

በአሸባሪው ሕወሓት ወረራ እና ጥቃት ለተፈናቀሉ የአፋር ክልል ወገኖች ድጋፍ ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሮቹ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።