ሰኔ 11 / 2013 (ዋልታ) – በአፋር ክልል በቀጣይ ሰኞ ለሚካሄደው 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት እየተከናወነ ነው።
በክልሉ ምርጫው በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ስርጭቱ በቀጣይ ሁለት ቀናትም እንደሚቀጥል በኢትዮጽያ ምርጫ ቦርድ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጣሀ አሊ ለዋልታ ተናግረዋል።
በክልሉ ከ2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበዋልም ነው ያሉት።
በአፋር ክልል ለክልሉ ምክር ቤት እንዲሁም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 11 የፖለቲካ ፓርቲዎች ይፎካከራሉ።
የአፋር ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አህመድ ከሎይታ በበኩላቸው ምርጫው በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የክልሉ መንግስት ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እየሰራ ነው ብለዋል።
በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለአፋር ክልል ምክር ቤት በ25 የሞርጫ ክልሎች እንዲሁም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6 የምርጫ ክልሎች ነው ምርጫው የሚካሄደው።
በበሀይሉ ጌታቸው