በአፋር ክልል በሕገ ወጥ መንገድ የተደበቁ 15 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ሰኔ 21/2014 (ዋልታ) ከጋላፊ እስከ ሰርዶ በየመንገዱ ዳር ተደብቆ የቆዩት 15 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በተጨማሪም አንድ ቦቴ ጫካ ውስጥ ነዳጅ ሲቀዳ እጅ ከፍንጅ ተይዟል ነው የተባለው፡፡

ዘመቻ ከተጀመረ ጌዜ ጀምሮ በየቦታው ተደብቀው የቆዩ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች መንቀሳቀስ መጀመራቸው ተመላክቷል፡፡

በዚህም ባለፉት ሦስት ቀናት በነዳጅ እጥረት ምክንያት ተዘግቶ የነበሩ የሰመራ ነዳጅ ማደያዎች ሥራ መጀመራቸውን ኤፍቢሲ የአፋር መገናኛ ብዙኃንን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW