በአፋር ግንባር የተገኘው ድል

ጳጉሜ 1/ 2013 (ዋልታ) የአፋር ልዩ ኃይል፣ ሚሊሺያ እና ሕዝባዊ ሰራዊት አሸባሪውን የሕወሓት ቡድን ከኡዋ ወረዳ በማስወጣት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ማድረጋቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።
በክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ በኩል የወጣው መግለጫ የሽብር ቡድኑ በፈንቲ ረሱ ያሎ በኩል ድንገተኛ ወረራ በማካሄድ ንፁሀንን በመጨፍጨፍ ወደ አፋር ክልለ ሰርጎ መግባቱን አስታውሷል።
ሰርጎ ከገባም በኋላ ሕዝብ ውስጥ በመመሸግ የቆየ ሲሆን የአፋር ልዩ ኃይል፣ ሚሊሺያ እና ሕዝባዊ ሰራዊት ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመተባበር ተጨማሪ የሕዝብ ጉዳት ሳይደርስ ስፍራውን ከቡድኑ የሚፅዳት ሥራ ሲከውን ቆይቷል።
በዚህ ሂደትም በዛሬው ዕለት የሽብር ቡድኑን ከወረዳው ጠራርጎ ማስወጣት መቻሉን የገለፀው ክልሉ ቡድኑ በማይሆን ስሌት ለአፋር ሕዝብ ያነሰ ግምት ይዞ ቢነሳም ወረራ ባካሄደባቸው ሁሉም ግንባሮች ከባድ የሆነ ሽንፈትና ኪሳራ እየገጠመው ነው ብሏል።