በኢትዮጵያ አዘጋጅነት የሚካሄደው የአፍሪካ ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ሻምፒዮና ተጀመረ

ጥር 16/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ አዘጋጅነት የሚካሄደው 11ኛው የአፍሪካ ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ሻምፒዮና በአዲስ አበባ ራስ ኃይሉ ጂምናዚየም ዛሬ ተጀመረ።
በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እና የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነትን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በሻምፒዮናው ላይ በወንዶች አዘጋጇ ኢትዮጵያን ጨምሮ አልጀሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ግብፅ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንዲሁም በሴቶች ደግሞ ኢትዮጵያ፣ አልጀሪያና ደቡብ አፍሪካ ይሳተፋሉ።
ሻምፒዮናው በዓለም ዐቀፍ ደረጃ በዱባይ አዘጋጀነት ለሚካሄደው የዓለም ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ውድድር አፍሪካን የሚወክሉ አገራት የሚለዩበት እንደሆነም ተገልጿል።
ሻምፒዮናው እስከ ጥር 21 ቀን 2014 ይቆያል።