በኢትዮጵያ ዘመናዊ የእንስሳት ህክምና እና እርባታ አለመኖሩ ተገለጸ

                                                             የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጣሰው ወልደሃነ (ፕሮፌሰር)

መስከረም 30/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በቀንድ ከብት ሀብት ቀዳሚ ብትሆንም ከዘርፉ መጠቀም ያልቻለችው ዘመናዊ የእንስሳት ህክምና እና እርባታ ባለመኖሩ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጣሰው ወልደሃነ (ፕሮፌሰር) ተናገሩ።

ፕሬዝዳንቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር ካሉ 12 ኮሌጆች አንዱ በሆነው በቢሾፍተ የእንስሳትና ግብርና ኮሌጅ ተገኝተው በዘርፉ የሰለጠኑ ተማሪዎችን አስመርቀዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ ከእንስሳት ሀብቷ እንድትጠቀም በዘርፉ የሚያሰለጥኑ ተቋማትና የምርምር ስራዎችን መደገፍ ያስፈልጋል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንስሳትና ግብርና ኮሌጅ በዚህ ረገድ አበረታች ስራዎችን እየሰራ ስለመሆኑም አንስተዋል።
ኮሌጁ ከመማር ማስተማር ተግባሩ በዘለለ ለአካባቢው ማህበረሰብ እንስሳትን በማከምና ግንዛቤ በመስጠት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አመልክተዋል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተቀበለው አቅጣጫ መሰረት በድህረ ምረቃና በምርምር ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረጉ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን በአለምአቀፍ ደረጃ ተመራጭ እንዲሆን የሚያደርግ ነውም ብለዋል።
በመስከረም ቸርነት